ለኢትዮጵያ ሰላም በጋራ እንስራ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ለኢትዮጵያ ሰላም በጋራ እንስራ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN- ሰኔ 03/2017

ለኢትዮጵያ ሰላም በጋራ እንስራ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ላይ ተናግረዋል።

ሰላም ወሳኝ ነገር መሆኑን ገልፀው ለዚህም መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል ።

ይሁንና 60 በመቶ የኢትዮጵያን ሰላም የምያናጋው ባለሀብቱ ነው ፣ ይህም የሚገለፀው ፀጥታን ለሚያውኩ አካላት በሚያደርገው ድጋፍ መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም በጫካ መሽገው ሀገርን ሰላም ለማሳጣት ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ባለሀብቱ የገንዘብ ድጋፍ ባለማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ሰላምን ለማምጣት በጋራ መሥራት ተገቢ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ራዕይ ይኑረን፣ ይህ ሲሆን ሀገር እናተርፋለን፣ ትውልድንም እናሻግራለን ብለዋል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review