የእሳት ሰደጋ ሰራተኞችን በማየት አባዜ የተያዘ 26 አመት ጀምስ ብራውን የተባለ እንግሊዛዊ ሰው የእሣት አደጋ ተከላካዮችን ለማየት በአንድ ሌሊት ሁለት ጊዜ ቤቱን አቃጥሏል።
በመስከረም 9/2023 ምንም እንኳን ከመጀመሪያው አደጋ በኋላ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለአደጋው መንስኤ ነው የተባለን የኤሌክትሪክ ሃይል ቢያቋርጡም የኤሌክትሪክ ብልሽቶችን እንደ መንስኤ በመጠቀስ ሃሰተኛ የሆኑ ሁለት የእሳት አደጋዎችን ሪፖርት ማድረጉ ተዘግቧል።
የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ በስፍራው ሲደርሱ እነርሱን መቅረፅን ጨምሮ ያሳየው ያልተለመደ ባህሪ ጥርጣሬን አስነስቶ በቁጥጥር ስር እንዲውልና የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ ተድርጓል።
ከእሳት ይልቅ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን በማየት አባዜ የተጠመደው ብራውን በአንድ አመት ውስጥ 80 ጊዜ ወደ ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ደውሎ እንደነበር ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
ብራውን ህይወትን አደጋ ላይ በመጣል እና በቸልተኛነት የተከሰሰባቸውን ሁለት ክሶች ያመነ ሲሆን የስምንት ወር እገዳ እና የ 150 ሰአታት ያለክፍያ ስራ ተፈርዶበታል።