ለኦሮሚያ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ድጋፍ ተደረገ

You are currently viewing ለኦሮሚያ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ድጋፍ ተደረገ

AMN- ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተሰበሰበ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ለኦሮሚያ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ተበርክቷል።

በድጋፍ መርሐ-ግብሩ የተገኙት የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሰቢ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ በነገዉ ሀገር ተረካቢ ትዉልድ ላይ መስራት የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ መረዳዳቱ እና መደጋገፉ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የኦሮሚያ ልማት ማህበር ከሚያስተዳድራቸዉ የልማት ድርጅቶች መካከል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ በማስተማር ይታወቃሉ፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ኢተቻ፣ የልማት ማህበሩ ባለፉት 33 ዓመታት በትምህርት፣ በጤና፣ በንፁህ መጠጥ ዉሀ እና በምግብ ራስን ከመቻል ጋር በተገናኘ በአባላቱ እና በህዝብ ተሳትፎ ሰፊ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ከመንግስት መዋቅሮች፣ ከባለሀብቶች የተሰበሰበ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና ለተማሪዎቹ ለምግብነት የሚውል የአይነት ድጋፍም የልማት ድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ድጋፎቹን ላበረከቱ የኦሮሚያ ክልል ተቋማት እና ባለሀብቶች የዕውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀትም ተበርክቶላቸዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review