
AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም
በከተራ እና ጥምቀት በዓል የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ታቦት ማለፊያ የሆነው የአንዋር መስጅድና የራጉኤል ቤተክርስቲያ አካባቢ መንገዶችን የማፅዳትና አስፓልት ማጠብ ስራ ተካሄደ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ የሚከበረውን የከተራ እና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው አካባቢና መንገዶቹን የማፅዳትና አስፓልት የማጠብ ስራ የተከናወነው።
የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አቶ ዮናስ ስዩም የጥምቀት እና የከተራ በዓል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ የሚያከብረው የአብሮነትና የወንድማማችነት መግለጫ ነው ብለዋል፡፡
በዛሬው የጽዳት ዘመቻም በርከት ያሉ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ወጣቶች ተሳትፈዋል ፡፡

የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮችም በከተራም ሆነ በጥምቀት በዓል ታቦት ወጥቶ እስኪገባ ከክርስቲያን ወገኖቻችን ጎን አንለይም ብለዋል ፡፡
በሀገራችን በርካታ ጉርብትና ያላቸው መስጂድ እና ቤተክርስቲያናት መኖራቸውን ያመለከቱት አስተያየት ሰጪዎቹ ይህም የትስስር እና የአብሮነታችን ማሳያ ነው ብለዋል።

Like
Comment
Share