ለውጡ ተሸፍነው የነበሩና ዓለም በቅጡ ሳይረዳቸው የኖሩ ሃብቶቻችን ብቅ ብለው እንዲታዩ እና እንዲከበሩ እድል ፈጥሮልናል ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።
የቱሪዝም ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞች ትናንት ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል ርዕሰ የፓናል ወይይት አካሂደዋል።
በፓናል ውይይቱ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ለውጡ እንደ ቱሪዝም ዘርፍ የተመለከተው፤ ትኩረት የሰጠው ሌላ ዘርፍ አለ ማለት ይከብዳል ብለዋል።
ቱሪዝም ከጎብኚዎች ቁጥር መጠን አንፃር ብቻ ሳይሆን ከሃገረ መንግስት ግንባታ እና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ትውልድ ከመፍጠር አንፃር ያለውንም ትልቅ ሚና ከግምት ያስገባ መሆኑን ገልጸዋል።
በሀገራዊ ለውጡ የተገኙ ትሩፋቶችን የሚዘክር መወያያ ሰነድ በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሽ ግርማ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።