የ28 ዓመቱ የትሪኒዳድና ቶቤጎው ወጣቱ ሙዚቀኛ ጆሹዋ ሬግሪሎ ስቲልፓን ወይም የብረት ከበሮ ለተከታታይ 31 ሰዓታት ሳያቋርጥ መጫወት በመቻሉ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ስሙን ማስፈር ችሏል፡፡
ከ5 ዓመቴ ጀምሮ ከበሮ እጫወት ነበር የሚለው ወጣቱ አባቴ የሙዝቃ ባንድ የነበረው በመሆኑ በሙዚቃ ተከብቤ ነው ያደኩት ብሏል፡፡
አብሮኝ ያደገ እንጂ በአንድ ጀንበር የመጣ አለመሆኑም ለዚህ ድል አብቀቶኛል ሲል ለዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ተናግሯል፡፡
በርግጥ የሙዚቃ መሳሪያውን ለ30 ሰዓታት ብቻ ለመጫወት አቅዶ የነበረ ቢሆንም የመድረክ ማናጀሩና በዙሪው ድጋፍ በሚሰጡ ሰዎች ታግዞ 31 ሰዓታትን ከበሮውን እየደለቀ ተጉዟል፡፡ በዚህም የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ለመሆን በቅቷል ሲል ዩፒአይ አስነብቧል፡፡