የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት አዲስ አበባ እጅግ በጣም ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች የምትገኝ ከተማ መሆኗን ገልፀው ለነዋሪዎቿ እና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ተመራጭ ትሆን ዘንድ በልማቱ ብቻ ሳይሆን በሰላም፣ ደህንነት፣ ህግ እና ስርዓትን በማስከበር ረገድም ውጤታማ ስራዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ የተመረቃችሁ እና ስምሪት የወሰዳችሁ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮቻችን፣ ዋነኛው የሰላም ባለቤት ከሆነው የከተማችሁ ህዝብ ጋር በመሆን የተጣለባችሁን ታላቅ እምነት ይዛችሁ በንድፈ ሀሳብና በተግባር በቀሰማችሁት እውቀትና ክህሎት ህዝባችሁን በቅንነት፣ በታማኝነትና በአገልጋይነት መንፈስ ማገልገል ይጠበቅባችኋል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡