ሉሲዎቹ ለ2026ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

You are currently viewing ሉሲዎቹ ለ2026ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

AMN-የካቲት 14/2017 ዓ.ም

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከዩጋንዳ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ዛሬ በዩጋንዳ ናኪቭቡ ሀምዝ ስታዲየም ከቀኑ 10:00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ካሜሮናዊቷ ዳኛ ማሪ ጆሴፊን በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ታውቋል።

ብሔራዊ ቡድናችን በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ እየተመራ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቷል ።

በዛሬው ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ ሲገባ ዩጋንዳዎች ቀይ መለያ የሚለብሱ መሆኑን ታውቋል።

በዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመልስ ጨዋታ የፊታችን የካቲት 19 ይደረጋል።

በጃዕፈር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review