ላለፉት 5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የጆርካ አዲስ አበባ አትሌቲክስ ውድድር ፍጻሜውን አገኘ

You are currently viewing ላለፉት 5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የጆርካ አዲስ አበባ አትሌቲክስ ውድድር ፍጻሜውን አገኘ

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

ላለፉት 5 ቀናት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የጆርካ አዲስ አበባ አትሌቲክስ ውድድር ጥሩ ልምድ የተገኘበት መሆኑን የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

በውድድሩ 20 ክለቦች እና ከ900 በላይ ትሌቶች በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች መሳተፋቸው ተመላክቷል።

በውድድሩ ክለቦች በቂ ዝግጅት በማድረግ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉበት እንደነበርም ተገልጿል።

በውድድሩ ውጤታማ እና ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶች የተገኙበት እንደነበርም ተመላክቷል።

በውድድሩ በአጠቃላይ በአንደኛ ዲቪዚዮን በወንድ እና በሴቶች መቻል የስፖርት ክለብ በሁለተኛ ዲቪዚዮን ደግሞ አራዳ ክፍለ ከተማ አሸናፊ በመሆን ዋንጫ አግኝተዋል።

ውድድሩ በቂ ዝግጅት የተደረገበት እና ውጤታማ እንደነበርም ፌደሬሽኑ ገልጿል።

በተለያዩ የአትሌቲክስ የፍጻሜ ውድድሮች አሸናፊ ለሆኑ ክለቦች እና አትሌቶች የሜዳሊያ፣ የገንዘብ እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review