AMN – ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
ሌላኛው ኢትዮጵያ የምትደምቅበት “AFRICA CELEBRATES-2024!” የተሰኘ ሁነት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መጀመሩን የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሣ ገለጹ።
ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የአፍሪካ የንጉሳውያን ሥርዓት መሪዎች፣ የቢዝነስ አንቀሳቃሾች፣ የፈጠራ ሰዎች፣ የጥበብ እና ፋሽን ባለሙያዎችን ያሳተፈው “AFRICA CELEBRATES-2024!” በአዲስ አበባ በቅርቡ ታድሶ በተከፈተው አፍሪካ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል” ብለዋል።
በዚህ ሁነት የአህጉሪቱ ባለሙያዎች ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡበት እና ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችንም የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንፃ ውስጥ መከፈቱን ነው ያስታወቁት።
የአፍሪካ MICE ቱሪዝም ማዕከሏ አዲስ አበባም በምትታወቅበት ድምቀት እንግዶቿን እያስተናገደች ትገኛለችም ብለዋል።