ሕብረተሰቡ መንግስታዊ አገልግሎትን በአቅራቢያው እንዲያገኝ በመደረጉ ዘርፈ ብዙ ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል- የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

ሕብረተሰቡ መንግስታዊ አገልግሎትን በአቅራቢያው እንዲያገኝ በመደረጉ ዘርፈ ብዙ ስኬት ማስመዝገብ መቻሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ውይይት “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተካሄዷል።

ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተ በኋላ ክፍለ ከተማው ራሱን ችሎ በመውጣቱ ሕብረተሰቡ መንግስታዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት መቻሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ገልጸዋል።

ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ የከተማ ግብርና ስራዎችን ጨምሮ በክፍለ ከተማው ዘርፈ ብዙ ስኬት መገኘቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

የቅድመ ጉባኤ ውይይት ተሳታፊ አባላትም ፓርቲው የጀመራቸውን እና ቃል የገባቸውን ስራዎች አሳክቷል ከዚህም የበለጠ እንዲሰራ እናደርጋለን ብለዋል።

በቀጣይም በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካዊ ዘርፍ መሰራት የሚገባቸው ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል እና ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጉባኤው አጋዥ መሆኑም ተጠቁሟል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review