AMN- መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
ሕብረተሰቡ በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮችና አምራች ዘርፎች ላይ ጥያቄዎቹንና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን እንዲያቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በዚሁ መሠረት ሕብረተሰቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች አማካኝነት ጥያቄዎቹን መላክ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡበት ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።