AMN – ታኀሣሥ 29/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመገኘት ከአቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ከተጋለጡ ነዋሪዎች ጋር ማዕድ ተጋርተዋል::
ከንቲባዋ መርሐግብሩን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በዓልን ከአቅመ ደካሞች ጋር አብሮ ማክበር ፤ የተቸገሩትን ዝቅ ብሎ መመልከት ነባር ኢትዮጵያዊ ባህል እና የብልፅግና መለያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ በሚገኙ 22 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በአሉን ከአቅመ ደካማ እና የሀገር ባለዉለታ ወገኖች ጋር የማክበር መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል::
“መላው የከተማችን ነዋሪዎች በዓሉን ስናከብር በፍቅር፣ በመተሳሰብና በአብሮነት መንፈስ ለሌላቸው በማጋራት እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል::

All reactions:
7979