መሬት በሊዝ ጨረታ ወስደው በወቅቱ ግንባታ ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ እርምጀ ተወሰደ

You are currently viewing መሬት በሊዝ ጨረታ ወስደው በወቅቱ ግንባታ ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ እርምጀ ተወሰደ

AMN- ጥር 14/2017 ዓ.ም

መሬት በሊዝ ጨረታ ወስደው በወቅቱ ግንባታ ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ እርምጀ መወሰዱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም የእቅድ መገምገሚያ ነጥቦች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አንዱ አለም ይጥላ ገልፀዋል፡፡

የካቢኔ ውሳኔ ከመፈፀም ፤ የሊዝ ገቢ ከመሰብሰብ እና መደበኛ የይዞታ መስተንግዶ ስራዎችን ኃላፊው በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡

መሬት በሊዝ ጨረታ ወስደው በወቅቱ ግንባታ ላላጠናቀቁ 19 አልሚዎች የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም አያይዘው ገልፀዋል፡፡

በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ውስንነቶችን በማረም እና የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋት በቀጣይ ቀሪ ወራቶች የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የይዞታ አገልግሎትን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦንላይን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የመሬት ሊዝ ጨረታ እና የመሬት ባንክ አገልግሎትን ለማዘመን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስለመጠናቀቃቸውም መገለጹን ከአዲስ አበባ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review