መስፈርት አማልተው ባልተገኙ 85 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
የባለስልጣኑ ቁጥጥርና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ኢሮ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጹት፤ መስፈርት አማልተው ባልተገኙ 85 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡
ከ375 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገው ክትትል በ85ቱ ላይ በተገኘ ጉድለት ከትምህርት ሥርዓቱ እንዲወጡ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
47 ተቋማት የተቀመጠውን አሠራር ጥሰው በመገኘታቸውም ከከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እስከ ሙሉ በሙሉ ከዘርፉ እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን ከ2 እስከ 4 ዓመት ድረስ ፍቃድ እንዳያገኙም መደረጉን አብራርተዋል፡፡
የተሰጣቸውን ቅጣት የማያከብሩ ተቋማት ደግሞ በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
ከተሰጣቸው የተማሪ ቁጥር በላይ የሚያስተምሩ ኮሌጆች መኖራቸውን አንስተው ይህም በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ጉድለት ማስከተሉን ተናግረዋል፡፡ 40 ተማሪ እንዲያስተምሩ ተፈቅዶላቸው 5ሺ ተማሪ ተቀብለው ከአቅማቸው በላይ የሆነ ተግባር የሚፈፅሙ መኖራቸውን አክለዋል፡፡
ህጋዊ ያልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች ወደ ተቋሙ እንደሚመጡ የተናገሩት ኃላፊው አሁን ላይ እነዚህ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በአግባቡ የተማረ ሰው የልፋቱን እንዳያጣ እና ተጭበርብረው የመጡ ሰነዶች ደግሞ አልፈው እንዳይገኙ በጥንቃቄ እነሠራለን ብለዋል፡፡
መሰል የማጭበርበር አካሄዶችን ለመግታት አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን የተማሪ ማስረጃዎች በዲጂታል ሥርዓት መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡ አሠራሩ የትምህርት ማስረጃዎችን በአግባቡ የማረጋገጥ ሂደት ላይ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል፡፡
በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ አጣርተን ጨርሰናል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ውጤቱን ለመንግስት የማቅረብ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ያልተሟላ እና ህጋዊ ባልሆነ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው በሥራ ላይ ያሉ መኖራቸውንም አክለዋል፡፡
ተቋሙ በማጣራት ሂደት ያገኘውን ውጤት የሚያሳውቅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ውሳኔው ግን የመንግስት ይሆናል ነው ያሉት፡፡
በፌደራል ተቋማት ላይ ሥራው መጠናቀቁን ገልጸው በቀጣይም በመጀመሪያ ምዕራፍ በኦሮሚያ ክልል፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ክልል ላይ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ትምህርት እንደ ንግድ ተቆጥሮ ሲሰራ የነበረበት አካሄድ ከእንግዲህ እንደማይኖርም ነው ያስገነዘቡት፡፡
በማሬ ቃጦ

See insights and ads
All reactions:
5050
8
7
Like
Comment
Share