መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው -አምባሳደሮች

You are currently viewing መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው -አምባሳደሮች

AMN – ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና በርካታ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተናገሩ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ጎብኝተዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

በዛሬው እለትም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ማዕከሉን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አይን ገላጭ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት ማዕከል ለመፍጠር ምን ዓይነት ዝርዝር ዕቅድና ጥናት እንዳደረገ የሚያሳይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያዊያን መልማቱ አስደናቂ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም የመረጃ ሉአላዊነትን የሚያረጋግጥ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በማዕከሉ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች በአጠቃላይ አስደሳች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ አገልግሎቱም ፈጣን መሆኑን ለመመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል።

ማዕከሉ የአገልግሎት ተደራሽነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አክለዋል።

በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን በበኩላቸው፥ በማዕከሉ የተመለከቱት ስራ አስደናቂ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ማካካስ ከማይቻሉ ነገሮች መካከል ጊዜ አንዱ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review