የአሰራር ስረአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር ነው፡፡
አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት አስራ ሁለት የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን አርባ አንድ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም አቅርበዋል፡፡ አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባ እና ሌሎችንም አካትተዋል። በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ የ12 ተቋማት 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህም ፡
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።
ምንጭ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት