መከላከያ ታላቅ አቅም ያለው አንጋፋ ተቋም በመሆኑ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ከዚህ በላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል – ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

You are currently viewing መከላከያ ታላቅ አቅም ያለው አንጋፋ ተቋም በመሆኑ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ከዚህ በላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል – ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

AMN – መጋቢት 30/2017

መከላከያ ታላቅ አቅም ያለው አንጋፋ ተቋም በመሆኑ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ከዚህ በላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገለጹ።

የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አድርጓል።

የሚኒስቴሩ እቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ፈይሳ ታደሰ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት በዘጠኝ ወራቱ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።

ሠራዊቱን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሀድ በአስተማማኝ መልኩ ሠላምን እንዲጠብቅ በማድረግ በኩል አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል።

የኢንዱስትሪዎችን አቅም በማሳደግ፣ወታደራዊ ዲፕሎማሲውን ከፍ በማድረግ፣ የሰው ሀብት አቅምን በማደራጀት እና በማዘመን፣በሀገር ውስጥ እና በውጭ ትምህርታዊ፣ ሙያዊ እና ወታደራዊ ስልጠናዎች የመስጠት ሥራዎች በዘጠኝ ወራቱ የተከናወኑ ተግባራት ናቸው።

የተቋሙን ገፅታ መገንባት፣የሙስና ወንጀሎችን መከላከል፣ለደንበኞች ፍትሀዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት፣ የስርዓተ- ፆታን ግንዛቤ ማሳደግ በአጠቃላይ ተቋሙ በተሰማራባቸው የስራ ዘርፎች አበረታች ውጤት መገኘቱ በውይይቱ ተገልጿል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች የተሠራው አጠቃላይ ሥራ ውጤታማና የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀሪው የሩብ ዓመት ይበልጥ የተሻለ የእቅድ አፈፃፀም ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፈፃሚ አካላት የተቋሙን ታላላቅ ግቦች መሰረት ያደረገ የእቅድ አፈፃፀም ውጤት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

መከላከያ ታላቅ አቅም ያለው አንጋፋ ተቋም በመሆኑ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ከዚህ በላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review