የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር የማዕከልና የክፍለ ከተማ አመራሮች በየካ ክፍለ ከተማ ጨለማ ቦታን ወደ ብርሀን የቀየሩ ብሎኮችና ቀጠናዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡
በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማዋ ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል ብለዋል።
በየካ ክፍለ ከተማ በርካታ ወንጀሎች ይፈፀምባቸው የነበሩ ጭለማ ስፍራዎች ወደ ብርሃን መቀየራቸውን ተመልክተናል ያሉት ሀላፊዋ በዚህም ማህበረሰቡ የደህንነት ስጋት ሳይኖርበት መንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
የፀጥታ ስራ ለተወሰነ አካል የሚተው ጉዳይ አለመሆኑንም አክለዋል።

ህብረተሰቡ ለሰላም እያደረገ ላለው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በመስራት እንደ ወትሮው የሰላም ባለቤትነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል።
ይህ መልካም ተሞክሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ፣ ክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የሰላም ሰራዊት አባላት እየሰሩት ላለው አበረታች ተግባርም ምስጋና አቅርበዋል።
በመሀመድኑር አሊ