የሬይ-ባን (Ray Ban) ሜታ መነጽሮች በቅርቡ በሕንድ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
ስማርት መነጽሮቹ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓኒሽ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎችን መተርጎም ከመቻላቸውም ባሻገር ተጠቃሚዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄ መረጃ መስጠት እና መዚቃ ለማድመጥ ያስችላሉ ተብሏል፡፡
መነጽሮቹ ከኩባንያው የኢንስታግራምና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መልዕክቶችን፣ ፎቶዎችን፣ የድምፅ እና የቪድዮ ጥሪዎችን በቀጥታ መቀበልና መላክ እንደሚያስችሉ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡
ኩባንያው ሜክሲኮ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መነጽሮቹን በቀጣይ ተደራሽ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ከአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡