ሜታ የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት ለቻይና አሳልፎ ሰጥቷል – የቀድሞ የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊ

You are currently viewing ሜታ የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት ለቻይና አሳልፎ ሰጥቷል – የቀድሞ የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊ

AMN – ሚያዝያ 02/2017

ሜታ የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት ለቻይና አሳልፎ መስጠቱን የቀድሞ የፌስቡክ የዓለም አቀፍ የህዝብ ፖሊሲ ዳይሬክተር ሳራ ዊን-ዊሊያምስ ተናግረዋል።

የቀድሞ ዳይሬክተሯ ሜታ በቻይና የ18 ቢሊየን ዶላር ንግድ ለማደርጀት የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት አሳልፎ መስጠቱን በኮንግረስ ችሎት ፊት ቀርበው መስክረዋል።

ሜታ ለቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የአሜሪካ እና የሌሎች ሀገራት የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ መመልከት የሚያስችል የይለፍ ፈቃድ በልዩ ትዕዛዝ መስጠቱንም ገልጸዋል።

የፌስ ቡክ አስተዳዳሪ ካምፓኒው የቀድሞ ዳይሬክተሯ ለአሜሪካ ሴናተሮች የሰጡትን ምስክርነት “በሐሰት የተሞላ” ሲል ተከራክሯል።

የሜታ ቃል አቀባይ ሪያን ዳንኤል የቀድሞ ዳይሬክተሯ ምስክርነት “ከእውነታው የተፋታ እና በውሸት የይገባኛል ጥያቄዎች የተሞላ ነው” ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቃል አቀባዩ የሜታ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ኩባንያው በቻይና አገልግሎቶቹን የማቅረብ ፍላጎት እንዳለው በይፋ ከመናገራቸው ውጪ አስካሁን በሀገሪቱ ሥራ አለመጀመሩን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review