ምክር ቤቱ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን የአዋጅ ማሻሻያ አጸደቀ

You are currently viewing ምክር ቤቱ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን የአዋጅ ማሻሻያ አጸደቀ

AMN ሰኔ 10/2017

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል የቀረበውን አዋጅ ማሻሻያ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 37ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሜቴ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ ከነባር አዋጁ 780/2005 በ58 አንቀጾች 14ቱ ላይ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በአዋጁ ማሻሻያ መደረጉ ለአገሪቱ የበለጠ ጠንካራ ህግ የሚያስፈልግ በመሆኑ ተገቢ ነው ብለዋል።

በአንዳንድ አንቀጾች ላይ ለጸጥታ አካላት ከተሰጡ መብቶች፣ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር የወጣ ገንዘብን ማስመለሰ፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ የደገፉ ሰዎችን በህግ ከመጠየቅ አንጻር ማሻሻያው ምን ያህል ለመከላከል ያስችላል የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

የአዋጁ ማሻሻያ አለም አቀፍ የፋይናንስ ግብረ ሀይል ምክረ ሃሳብን መሰረት ያደረገ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል።

ምክር ቤቱ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል የቀረበውን የአዋጅ ማሻሻያ 1387/2017 ሆኖ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅን ለዝርዝር እይታ ለሰው ሀብት ልማት፣የስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review