
AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል።
ምክር ቤቱ አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን በማድረግ ላይ ይገኛል።
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርቧል።
ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።