ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ

AMN-ሚያዝያ 21/3017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።

“የደጋጎቹና የትጉሃኑ ከተማ እንዲሁም የሀገራችን የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነቺው ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ገብተናል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

በቆይታቸው በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም አስታውቀዋል።

ኮምቦልቻ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የደቡብ ወሎ ዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ለህብረተሰቡ ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review