
AMN ግንቦት 12/2017 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ሁለተኛው የብራዚል-አፍሪካ የምግብ ዋስትና፣ ረሃብን መዋጋት እና የገጠር ልማት ጉባኤ በብራዚሏ ዋና ከተማ ብራዚሊያ መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
መድረኩ የግብርና ምርትን እድገት፣ የገጠር ልማትንና የምግብ ዋስትናን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጓል።
ግብርናን በተሻለ መንገድ የሚመሩ የጥናትና ምርምር፣ አዳዲስና በቴክኖሎጅ የታገዙ አሰራሮችን የሚያሳልጡ ተቋማት ግንባታ በዘርፉ ከፍ ያለ እመርታ የሚያመጡ ናቸው።

ኢትዮጵያ በፖሊሲ የተደገፈ መሰረታዊ የለውጥ ስራዎችን በመተግበር የግብርናውን ዘርፍ ከፍ ባለ እመርታ ላይ ለማስገኘት የሰራችውንና እየሰራች ያለውን ተሞክሮ በጉባዔው ታቀርባለች የሌሎችንም ትጋራለች።
በመድረኩ የእውቀት ሽግግር እና የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም የምግብ ስርዓታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የመስክ ምልከታዎችን፣ የልምድ ልውውጦችንና ስምምነቶችን ማከናወን ቀጥለናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡