ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

AMN ግንቦት 26/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ በከፊል የተጣራ የአኩሪ አተር ዘይት የሚያመርተውን የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማዋ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በከፊል የተጣራ የአኩሪ አተር ዘይት የሚያመርተውን የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ኢንደስትሪው በ374 ሚሊዮን ብር የተገነባ ሲሆን በቀን 120 ቶን የአኩሪ አተር ዱቄት እና በከፊል የተጣራ የምግብ ዘይት የማምረት አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቲቲኬ ኢንደስትሪ ፋብሪካ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለጀመርነው የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት አንድ ሁነኛ አብነት ነው ብለዋል።

ጎንደር ሰላምን በማስጠበቅና በማጽናት ልማትን የማረጋገጥ ለዕድገትም የመትጋት ደማቅ ማሳያ እንደሆነች መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review