AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
አቶ ተመስገን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት አቶ ቡልቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰላማዊ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ብለዋል።
አቶ ቡልቻ ለሀገር ሁለንተናዊ ጥቅም የሰሩና ለችግሮችም እራሳቸውን የመፍትሔ አካል አድርገው ጽናትን ያሳዩ ሰው ነበሩም ሲሉ አመልክተዋል፡፡
በጉምቱ ፖለቲከኛ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ያሉት አቶ ተመስገን ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ሲሉም አመልክተዋል።
ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድና ኢትዮጵያዊያን መጽናናትንም ተመኝተዋል፡፡