ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

ዛሬ ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በጉብኝታችን ወቅት ሁለቱ ሀገራት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ በቴክኖሎጂ እና ሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም አያሌ ዓመታትን የተሻገር ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር እያደገ ስለመምጣቱ ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review