AMN- የካቲት 24/2017 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፥ በአማራ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ባህርዳር ገብተዋል።
ባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ኢዜአ ዘግቧል።