ሞሐመድ ሳላህ የዓመቱ ኮከብ ተብሎ ተመረጠ

AMN-ግንቦት 01/2017 ዓ.ም

ሞ ሳላህ የእንግሊዝ እግርኳስ ፀሃፊዎች ማህበር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ።

የሊቨርፑሉ የመስመር አጥቂ በውድድር ዓመቱ በሊጉ 28 ግብ አስቆጥሮ 18 ወደ ግብነት የተቀየሩ ኳሶችን ማመቻቸት ችሏል።

ሊቨርፑል ከአራት ዓመት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ እንዲሆን ግብፃዊ ተጫዋች ትልቁን አስተዋጽኦ አበርክቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review