AMN – ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሸነፉበት የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ክስ አቅርበዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ ክሱ መሠረተ ቢስ ነው ሲል አስተባብሏል።
ሩሲያ በምርጫ ጣቢያዎች ቦምብ በመጣል የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማወክ እና ለማስተጓጎል ማቀዷን የሚያሳዩ ፍንጮች መገኘታቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል።
በተለያዩ ስቴቶች በሚገኙ ምርጫ ጣቢዎች ላይ ያነጣጠሩ የቦምብ ጥቃቶች ታስበው እንደነበር የአሜሪካ የፌዴራሉ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) አመልክቷል።
በምርጫ ጣቢያዎቹ ሽብር እና ማስፈራራትን በመፍጠር የምርጫ ሂደቱ በአግባቡ እንዳከናወን ለማድረግ የታሰበ እንደነበረም ኤፍ ቢ አይ ጠቅሷል።
ሩሲያ በበኩሏ ውንጀላው መሠረተ ቢስ እና ተጨባጭነት የሌለው ነው ማለቷን ሲኤንኤን ዘግቧል።