ሩሲያ እና ዩክሬን ለሰላም ድርድር እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት የአየር ጥቃት መለዋወጣቸው ተሰማ

You are currently viewing ሩሲያ እና ዩክሬን ለሰላም ድርድር እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት የአየር ጥቃት መለዋወጣቸው ተሰማ

AMN – ግንቦት 25/2017 ዓ.ም

ሩሲያ እና ዩክሬን ለሰላም ድርድር እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት የአየር ጥቃት መለዋወጣቸው ተገልጿል፡፡

የሩሲያ እና ዩክሬን ልዑካን ቡድን ከሰዓታት በፊት ለሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ተርክዬ በገቡበት ሰዓት ሁለቱም ሃገራት የቦምብ ድብደባዎችን ማድረጋቸዉ ተዘግቧል፡፡

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር 162 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙንና አብዛኛዎቹ ድሮኖች በአዋሳኝ ክልሎች ላይ የነበሩ መሆናቸዉን አስታዉቋል፡፡

ዩክሬን ከአንድ ቀን በፊት የሩሲያ ግዛት በሆነችዉ በሳይቤሪያ እና በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ሌሎች የጦር ሰፈሮች በፈጸመችዉ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ስትራቴጂካዊ ክሩዝ ሚሳኤል ተሸካሚዎችን መምታቷ ተገልጿል፡፡

ሩሲያም በአፀፋው በአንድ ሌሊት በ80 ሰዉ አልባ ድሮኖች ግዛቷን ኢላማ አድርጋ 12 ጥቃቶችን መሰንዘሯን ዩክሬን አስታዉቃለች ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review