AMN-የካቲት 27/2017 ዓ.ም
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የጁገል ዙሪያ የኮሪደር እና መልሶ ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።
የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቱ አካባቢውን በማስዋብ የተሻለ ገፅታን የሚያላብሱ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የልማት ሥራዎቹ በቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ አቅም በመሆን ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል።
በተለይ የኮሪደር ልማት ስራው የሐረር ከተማን ዕድገት ከማሳለጥ ባለፈ ለዜጎች ዘመናዊ የከተሜነት የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።
ፕሮጀክቱን በጥራት እና ፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ርብርብ እንደሚደረግም ማረጋገገጣቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።