“ሰላምና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በቡታጅራ ከተማ ተከፈተ

You are currently viewing “ሰላምና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በቡታጅራ ከተማ ተከፈተ

AMN – የካቲት- 6/2017 ዓ.ም

“ሰላምና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ ተከፈተ።

ከአውደ ርዕዩ በተጨማሪ በምዕራፍ ሁለት “ሰላም እና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይትም እንደሚካሄድ ታውቋል።

ድርጅቱ በምዕራፍ አንድ “ሰላምና ኢኮኖሚ ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የፓናል ውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

በምዕራፍ ሁለት በቡታጅራ ከተማ ዛሬ የሚካሄደው የፓናል ውይይት መድረክ አካል የሆነው የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) እና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መከፈቱን ኢዜአ ዘግቧል።

የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን፣ ባህላዊ እሴቶችን እና እምቅ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚያሳይ ነው።

በተጨማሪም ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የህዝብን አብሮነት ለማጠናከር የሚረዱ ባህላዊ የእርቀ ሰላምና የዳኝነት ሥነ ሥርአቶችን የሚያሳዩ ፎቶዎችም ለእይታ ቀርበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review