ሰሜን ኮሪያ እና ብሪክስ በዩክሬን የተኩስ አቁም ድርደር ላይ መሳተፍ አለባቸው -ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

You are currently viewing ሰሜን ኮሪያ እና ብሪክስ በዩክሬን የተኩስ አቁም ድርደር ላይ መሳተፍ አለባቸው -ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

AMN-መጋቢት 19/2017 ዓ.ም

ሰሜን ኮሪያ እና ብሪክስ በዩክሬን የተኩስ አቁም ድርድር ላይ መሳተፍ አለባቸው ሲሉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሳሰቡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ፣ ዩክሬን በተባበሩት መንግስታት ‘ጊዜያዊ አስተዳደር’ ጥላ ሥር በመሆን የሰላም ድርድሩ ሂደት አካል እንድትሆን ሀሳብ ማቅረባቸውን የሩሲያ መንግስት ሚዲያ ታስ ዘግቧል።

ፑቲን፣ በሩሲያ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ሙርማንስክ ወደብ ለሚገኙት የሰራዊት አባላት እንደገለጹት፣ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በሩሲያ የተጀመረውን የሶስት አመታት ጦርነት ለማስቆም እየተካሄደ ባለው የሰላም ድርድር ሂደት በርካታ ድንጋጌዎች መቀመጣጨውን መግለቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ፑቲን፣ ካቀረቧቸው ብዙ የሰላም አማራጭ መካከል በዩክሬን አዲስ ምርጫ እንዲካሔድ እና ሀገሪቱ በአለም አቀፍ አስተዳደር ስር ሆና “ቁልፍ ስምምነቶችን መፈረም” የሚሉት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልፃል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ እና በህዝቡ አመኔታ ያለው መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ፣ ከአዲሱ መንግስት ጋር ስለሰላም ስምምነት ለመነጋገር እንችላለን ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

ፑቲን፣ አክለውም ፒዮንግያንግን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ከአሜሪካ እና ከሩሲያ አልፎ በሰላሙ ሂደት ውስጥ መሳተፍ አለባቸው ማለታቸው የተመላከተ ሲሆን፣ ከአውሮፓ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውንም መረጃው አመላክቷል፡፡

እንደ ዩኤስ ዘገባ ከሆነ ደግሞ ኪየቭ እና ሞስኮ በጥቁር ባህር መርከቦች ላይ የሚደረጉ ወታደራዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የተስማሙ ቢሆንም፣ ባለፉት ቀናት ሁለቱም የሰላም ድርድሩን ቸላ በማለት አንዱ ሌላውን ሲከስ እንደተስተዋለም ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ዩክሬን የነዳጅ ዲፖዎቼን እና የኤሌክትሪክ ኀይል ማሰራጫዎቼን እና መሰረተልማቶችን ኢላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶች እያደረሰችብኝ ነው ስትል ሩሲያ ዩክሬንን እንደከሰሰች የተለያዩ ሚዲያዎችን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review