ሳምንቱ በታሪክ ውስጥ

ይህ መረጃ በሳምንት አንድ ቀን ዓለም በታሪክ ውስጥ ካስተናገደቻቸው ትላልቅ ክስተቶች መካከል ጥቂቶቹን መርጠን ወደ እናንተው የምናደርስበትና የምናስታውስበት ነው፡፡

ለዛሬም ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በታሪክ ከተመዘገቡ ሁነቶች መካከል የሚከተሉትን መርጠን ልናስታውስ ወደናል፤ መልካም ንባብ።

1. ኮፊ አናን፣ የተባበሩት መንግስታት ደርጅት የመጀመሪያው ጥቁር ዋና ፀሀፊ ሆነው የተሰየሙት እ.ኤ.አ ጥር 1 ቀን በ1997 በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር፡፡

ትውልደ ጋናዊው ኮፊ አናን፣ እ.ኤ.አ. ከ1997 እስከ 2006 ድረስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባተኛው ዋና ፀሀፊ ሆነው ያገለገሉ ታዋቂ ዲፕሎማት ሲሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ይህን ከፍተኛ ሀላፊነት ያገኙ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ እንደሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

አናን፣ በስልጣን ዘመናቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በተለይም በሰላም ማስከበር፣ በሰብአዊ መብቶች እና በዘላቂ ልማት ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይነገርላቸዋል፡፡

ለዚህ በጎ ስራቸውም እ.ኤ.አ. በ2001 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

2. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን የነጻነት አዋጅ ፊርማን የፈረሙት እ.ኤ.አ ጥር 1 ቀን በ1863 በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር፡፡

ይህ የነፃነት አዋጅ ፊርማ በወቅቱ በእርስ በርዕስ ጦርነት ክፉኛ ግጭት ውስጥ የነበሩ የአሜሪካ ህዝቦችን እና በስፋት ይካሄድ የነበረውን የባርነት ጭቆናን ለማስቀረት ጥበብና ብልሃት በተሞላበት መንገድ ወደ ሰላምና አንድነት ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ እንደነበር ይነገርለታል።

ይህ በፕሬዝዳንቱ የተፈረመው የነጻነት አዋጅ ህጋዊ ሰነድ ፣ ባርነትን ለማስወገድ የሞራል ቁርጠኝነትን ያመላከተ እና የእርስ በርስ ጦርነቱን በማስቀየር በኩልም ከፍተኛ አስተዋኦ እንደነበረው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

3. አስራ አንድ የአውሮፓ ሀገራት ዩሮን የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንዲሆን ያሳወቁት እ.ኤ.አ ጥር 1 ቀን በ1999 በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር፡፡

ዩሮን በጋራ ለመገበያያ ገንዘብ እንዲሆን የተፈለገበት ዋነኛ አላማ ግብይቶችን ለማቅለል፣ የዋጋ ግልጽነትን ለማሳደግ እና በአባል ሀገራቱ መካከል የኢኮኖሚ ትብብርን ለማስፈን እንደሆነ ነው የተመላከተው፡፡

ይህም በአህጉሪቱ ውስጥ የንግድ እና የኢኮኖሚ መረጋጋትን በማስፈን በኩል ትልቅ ምዕራፍ እንደከፈተ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ዩሮ፣ በአሁኑ ጊዜ ኮሶቮ እና ሞንቴኔግሮን ጨምሮ የ19 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ይፋዊ ገንዘብ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ምንጭ፡-የተለያዩ ሂስትሪ ቻናሎች

በአስማረ መኮንን

All reactions:

88

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review