ስኬት ባንክ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር ከመስጠት ባለፈ በስራቸው ስኬታማ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ኢትዮጵያ የያዘችውን የስኬትና የብልፅግና ጉዞ ፈጣን ለማድረግ ባንኩ በኢንዱስትሪ ዘርፉ በስፋት እየሰራ መሆኑ ተነስቷል።
ስኬት ባንክ ላለፉት 25 ዓመታት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እና ለአምራቾች የስራ እድሎችን በመፍጠር ለበርካቶች ህይወት መቀየር መሰረት መጣሉም ተመላክቷል።
ስኬት ባንክ አምራች ዘርፉን ለማገዝ እና በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ለመሆን በቴክኖሎጂ እና በሰው ሀይል እራሱን ማደራጀቱንም ገልጿል።
የእስከ አሁን ሂደቱን በተመለከተም “የፋይናንስ አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ምርታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
በንጉሱ በቃሉ