ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ

You are currently viewing ሾዴ የተባለው የሸኔው መሮ ዋና ሰው ተገደለ

AMN- መጋቢት 27/ 2017 ዓ.ም

ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የሸኔው መሮ ዋና ሰው እንደሆነ የሚታወቀው መገደሉ ተገለፀ።

የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድርድር ከጫካ ወጥቶ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ድረስ ከመሮ ጋር ተጉዞ የሸኔ ሽብር ቡድን ተደራዳሪ የነበረው ሾዴ በተወሰደበት እርምጃ ተገድሏል።

ሾዴ የተባለው የሽብር ቡድኑ አመራር ከታንዛኒያ መልስ የአጠቃላይ የወለጋ ዞኖች አዛዥ ተደርጎ በመሮ ተሹሞ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ሾዴ የተገደለው ምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ገንጂ አካባቢ ከኮርማ ወንዝ ወደ ሱጊ በሚወሰደው መንገድ ላይ በሞተር ሳይክል ተደብቆ ሲጓዝ የፀጥታ ኃይሎች ባገኙት መረጃ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እርምጃ ተወስዶበታል።

ከሾዴ ጋር አብረው አጅበው ሲጓዙ የነበሩ በርካታ የሸኔ ሽብር ቡድን አባላትም መደምሰሳቸውን ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሠሞኑ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በሌሎችም አካባቢዎች የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ክፉኛ እየተመቱ በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን የሸኔ ታጣቂዎች የመከላከያ ሠራዊቱን ምት መቋቋም ተስኗቸው እየተፍረከረኩ እጅ እየሠጡ እየተማረኩ እርምጃ እየተወሰደባቸውና እየተበተኑ ይገኛሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review