የቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ቀዳማዊት እመቤት ማዳም ነኹ በሃኖይ የሚገኘውን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የአይነስውራን ት/ቤት እንዳስጎበኟቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አስታውቀዋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በነበራቸው ጉብኝት በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኘው እና በተለያዩ ክልሎች እየተሰሩ ላሉት አዳዲስ የአይነስውራን አዳሪ ት/ቤቶች የሚሆኑ ተሞክሮዎችን ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡