ቆጥረን የተረከብነውን ስራ ቆጥረን ማስረከብ ይጠበቅብናል ፦ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing ቆጥረን የተረከብነውን ስራ ቆጥረን ማስረከብ ይጠበቅብናል ፦ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ቆጥረን የተረከብነውን ስራ ቆጥረን ማስረከብ ይጠበቅብናል ሲሉ አስገነዘቡ ፡፡

ምክር ቤቱ ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን የምክር ቤቱ አባላት እና አስፈፃሚዎች በተገኙበት ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።

በግምገማው መክፈቻው ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንዳሉት ዛሬ የሚገመገሙት ስራዎች ነገ ለሚካሄደው ጉባኤ ግብዓት ይሆናል።

የከተማ አስተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት የስድስት ወራት የመንግስት ስራዎች ሪፖርት አፈፃፀም በከተማው ፕላንና ልማት ቢሮ አቶ አደም ኑሪ እየቀረበ ይገኛል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ የምክር ቤቱ አባላትና ስራ አስፈፃሚዎች እንደሚወያዩበት ይጠበቃል።

በግምገማው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ፋኢዛ መሀመድን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላትና ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

በነገው ዕለትም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ/ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል ።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review