የህዝብን አንድነትና ሰላም በሚያሰፍን መልኩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢትዮጵያን ቋንቋና ባህል ይበልጥ ለዓለም ማስተዋወቅ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ሀላፊዋ ቢሮው ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ቋንቋና ባህልን ዘመኑ ከሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ይበልጥ ለዓለም ተደራሽ ለማድረግና የአገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥም ተቋማዊ ቅንጅት ፈጥሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
ሁለተኛው ከተማ አቀፍ የባህልና ቋንቋ ጉባኤ ”ቋንቋ፣ባህልና ቴክኖሎጂ ለዕድገት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን፤ ቴክኖሎጂን እንዴት ከባህል እና ከቋንቋ ጋር አስተሳስሮ ስራ ላይ ማዋል ይቻላል በሚል ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
አይናለም አባይነህ እና ፀጋ ታደለ