በሀረሪ ክልል በሆቴል፣ በማኑፋክቸሪንግና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ

You are currently viewing በሀረሪ ክልል በሆቴል፣ በማኑፋክቸሪንግና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል- አቶ ኦርዲን በድሪ

AMN-መጋቢት 14/2017 ዓ.ም

በሀረሪ ክልል በሆቴል፣ በማኑፋክቸሪንግና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት አካሂዷል።

በመድረኩም የኢንቨስትመንት ዝግጅትና ፍቃድ አሰጣጥ በሚመለከት ሰፊ ውይይት ተካሄዷል።

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፣ በክልሉ የተጀመረውን የኢንቨስትመንት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

በተለይም በራሳቸው ይዞታ ላይ ለሚያለሙ ባለሃብቶች ቅድሚያ በመስጠት የመደገፍ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ክልላዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፎች ላይ በተለይም በሆቴል፣ በማኑፋክቸሪንግና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት።

የመንግስት ተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዲጎለብት ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review