በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ ያለዉ ስራ አበረታች ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።
30ኛው የሜዲካል ላቦራቶሪ የሙያ ማኅበር ዓመታዊ ሳይንሳዊ ጉባዔና ዓለም አቀፍ የሜዲካል ላቦራቶሪ ባለሙያዎች ሳምንት “ላቦራቶሪ ሕይወት ያድናል” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የላቦራቶሪ አገልግሎት በግል እና በመንግሥት ተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ፈር ቀዳጅ ልምድ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
የኮቪድ ወረርሽኝም የላቦራቶሪ አቅምን ለማሳደግ መልካም አጋጣሚ እንደፈጠረ ነው ያመላከቱት፡፡
አሁንም ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ያመለከቱት ሚኒስትሯ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ ያለዉ ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
ከውጭ ይገቡ የነበሩ የህክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ደረጃም አበረታች ጅማሮ መኖሩን ማብራራታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።