በሀገር ውስጥ ምርቶች የመኩራት እና የመጠቀም ባህል እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

You are currently viewing በሀገር ውስጥ ምርቶች የመኩራት እና የመጠቀም ባህል እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

AMN – ሚያዝያ 06/2017

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛር መካሄድ ጀመረ፡፡

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ “የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለሀገራዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች መካሄድ ጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች፣ አምራች ኢንተርፕራይዞችና ባለድርሻዎች በተገኙበት በየካ ክፍለ ከተማ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ፣ በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጅ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ልጋኒ እንደገለጹት፣ በሀገር ውስጥ ምርቶች የመኩራትና የመጠቀም ባህላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ ይገባል ብለዋል።

ባዛሩ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በከተማ ደረጃ 1540 የሚደርሱ እና የየካ ክፍለ ከተማ ደግሞ 53 አምራች ኢንተርፕራይዞች በባዛሩ ምርቶቻቸውን አቅርበዋል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የምግብ ምርቶችና የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ባዛሩ እስከ ቅዳሜ እንደሚቆይ ተገልጿል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review