በሁኔታዎች የማይለወጠው የኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ

You are currently viewing በሁኔታዎች የማይለወጠው የኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 04/2017 ዓ.ም

በሁኔታዎች የማይለወጠው የኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከቻይና አፍሪካ መድረክ(ፎካክ) የአፈጻጸም ክትትል የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ተወያይተዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ያቀረቡትን ሰላምታ በቻይናው አቻቸው በኩል አድርሰዋል።

የኢትዮጵያና ቻይና በሁኔታዎች የማይለወጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነት በማጠናከር እና በ2024 የቤጂንግ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ያቀረቧቸውን የፎካክ አስር አጋርነት ተግባራትን በመተግበር ረገድ ትልቅ ለውጥ መመዝገቡን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሁለቱ አገራት አጋርነት በደቡብ ደቡብ ትብብር፣ በብሪክስ እና በተመድ እንዲሁም በሌሎችም መስኮች ጥሩ ማሳያ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

በቻይና፣ አፍሪካ እና የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የሦስትዮሽ አጋርነት በአዲስ አበባ የተከፈተው የኢንዱስትሪ የልሕቀት ማዕከል ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ዝመና ከፍተኛ ሚና የሚጫወት እና በአፍሪካ ቻይና ግንኙነት ላይ ጉልህ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑንም ሚኒስትሩ አንስተዋል።

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በበኩላቸው ከአሁን በፊት የሁለቱ አገራት መሪዎች የጋራ መግባባት የደረሱባቸውን መስኮች ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እና ቻይና የደቡብ ደቡብ ትብብር እና የብሪክስ ወሳኝ አባል መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ዋንግ ዪ ቻይና ኢትዮጵያን ሁነኛ አጋር እና ወዳጅ አድርጋ እንደምትመለከታት በመግለጽ የተሻለ ልማት እንዲመዘገብ አጋርነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review