242 ሰዎችን አሳፍሮ ከህንድ አህመዳባድ የተነሳው እና ወደ ለንደን ጋትዊክ አውሮፕላን ማረፊያ በረራ የጀመርው አውሮፕላን ብዙም ሳይርቅ ተከስክሷል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልጸው፣ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ከአየር መንገዱ 12 ሰራተኞች በተጨማሪ 169 የህንድ፣ 53 የብሪታኒያ፣ 1 የካናዳ እንዲሁም 7 የፖርቹጋል ዜጎች በአውሮፕላኑ ተሳፍረው እንደነበር ተዘግቧል።
አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ ከ90 በላይ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ተልከዋል።
የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይነት እንደሚሰጥ አየር መንገዱ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።