በህገወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዘው የነበሩ 70 የመስሪያ ቦታዎች ለ70 ኢንተርፕራይዞች ተላለፉ

You are currently viewing በህገወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዘው የነበሩ 70 የመስሪያ ቦታዎች ለ70 ኢንተርፕራይዞች ተላለፉ

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባለፉት 9 ወራት በህገወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዘው የነበሩ 70 የመስሪያ ቦታዎች ለ70 ኢንተርፕራይዞች መተላለፋቸዉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለAMN ዲጂታል ሚዲያ እንዳስታወቀዉ ባለፉት 9 ወራት ለብዙ ወጣቶች መሆን ሚችሉ ግን በአንድ ግለሰብ ተይዘው የነበሩ የመስሪያ ቦታዎችን ጨምሮ በስግብግብነት የመንግስትን ንብረት ወደ ግል ለማዞር ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን በመለየት እና በማስለቀቅ 70 የመስሪያ ቦታዎችን ለ70 ኢንተርፕራይዝና ለ235 ወጣቶችና ሴቶች ማስተላለፉን አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሌላ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ ቦታን በማስለቀቅ 6 ኢንተርፕራይዞችና 60 ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሼድ ግንባታ በመናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ክፍለ ከተማዉ ባለፉት 9 ወራት ለ26 ሺ 214 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review