በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 310 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 310 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN – ጥር 11/2017 ዓ.ም

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ለመመለስ በተሰራው ስራ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ 310 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ሀገር የተመለሱት 301 ሴቶች እና 9 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህፃናት ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ 83 ሴቶች፣ 3 ወንዶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 99 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 9 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 89 ሺህ 898 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተመርቀዋል መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review