በሎስ አንጀለስ ከተማ ከፊል የሰዓት እላፊ ገደብ ታወጀ

You are currently viewing በሎስ አንጀለስ ከተማ ከፊል የሰዓት እላፊ ገደብ ታወጀ

AMN- ሰኔ 4/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ 5ተኛ ቀኑን ያስቆጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዋ ከንቲባ ካረን ባስ ከፊል የሰዓት እላፊ ገደብ ማወጃቸው ተነግሯል።

የሎስ አንጀለስ ከተማ ከንቲባ ካረን ባስ 5ተኛ ቀኑን ባስቆጠረውና በሰነድ አልባ ስደተኞች ተቃውሞ በከተማዋ ለደረሰው ዝርፊያ፣ አለመረጋጋት እና ብጥብጥ ምላሽ ነው ያሉትን ከፊል የሰዓት እላፊ ገደብ አውጀዋል።

የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም፣ የሎስ አንጀለስ ከተማ ሁኔታን በማቀጣጠል በኩል ዶናልድ ትራምፕን ተጥያቂ አድርገዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ይህ ተቃውሞ በሰላም እና በህዝብ ስርዓት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው በማለት አውግዘዋል፡፡

ይህንንም ለመቆጣጠር የፈደራል መንግስት ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ከተማዋ ማሰማራቱ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በፈደራል መንግስት የሰፈሩት የብሔራዊ ዘብ አባላት ያለ እነሱ እውቅና መሆኑን የካሊፎርኒያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የሎስ አንጀለሱ ከንቲባ ካረን ባስ በበኩላቸው፣ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች አለመረጋጋቱን በማስቆም ተቃዋሚዎችን ለመበተን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ቢገልጹም፣ ኒውሰም በአንፃሩ በፌዴራል መንግስቱ ምላሽ ወቀሳ መሰንዘራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ቀጥሎ በትናንትናው ዕለት ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር የተጋጩባት ቺካጎን ጨምሮ በሌሎች ዋና ዋና የአሜሪካ ከተሞችም ሰልፎች መቀጠላቸው ተመላክቷል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review