በሕንድ ‘ማሃ ኩምብ’ በተሰኘ መንፈሳዊ በዓል ላይ በተከሰተ ግፊያ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

You are currently viewing በሕንድ ‘ማሃ ኩምብ’ በተሰኘ መንፈሳዊ በዓል ላይ በተከሰተ ግፊያ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

AMN – ጥር 21/2017 ዓ.ም

ዛሬ ማለዳ ላይ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሂንዱዎች በሰሜን ሕንድ በሚከበረው ‘ማሃ ኩምብ’ በተሰኘ መንፈሳዊ በዓል ላይ የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም እና ቀድሞ በወንዞች ውስጥ ለመነከር ሲጣደፉ በተፈጠረ ግርግር የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ብዙዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ክስተቱን “እጅግ አሳዛኝ” ያሉት ሲሆን፣ ለሟች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

የምን ያክል ሰዎች ህይወት እንዳለፈ ያልጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ፈጥነው እንዲያገግሙ ተመኝተዋል።

የኡታር ፕራዴሽ ግዛት ከፍተኛ ባለስልጣን ዮጊ አዲቲያናት በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣብያ በሰጡት መግለጫ፣ የሟቾችን ቁጥር በውል ባይገልፁም፣ በርካታ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና አንዳንዶቹም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ማመልከታቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ይሁን እንጂ በክስተቱ የ12 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review